የተስፋ ቃል
Yetesfa Qal
2015 · ትራክ 9 · 4:47 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የተስፋ ቃል ሰጠኝ ገና በልጅነት እኔ አለሁ አለኝ
ሃሩሩ እንዳይጐዳኝ እባቡ እንዳይነድፈኝ እንዳይጠጋኝ
አቤት የተነሳው የጠላት ዘመቻ ገፍቶ ሊጥለኝ
የእርሱ ቤት ደካማ የእኔ ግን በጌታ ሄደ እየበረታ
አዝማች · Chorus
የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር (፪x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ)
የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር (፪x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ)
የእኔ ዳኛ ከጐኔ ነበር (፪x) ከጐኔ (ከጐኔ ከጐኔ)
ገና (፫x) ገና ነው
ገና (፫x) ነው
ገና ነው የአባቴ ስራ
ገና ነው በእኔ የጀመረው
ገና ነው መቼ ተፈጸመ
ገና ነው ማነው ቆሟል ያለ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በእጄ ላይ ያለው በትር ከሆነማ ባሕሩን ምታው
ለአንተ መንገድ አለ ከሁኔታ በላይ አብ ያዘጋጀው
ዛሬ የከበደህ ያስደነገጠኽን የግብጹን ጦረኛ
በመዝሙር ልጣለው ጆሮዎችህን ስጠኝ ና ተባበረኛ
(አሃሃሃሃሃ) መንፈሱ በላዬ አሁን መጣብኝ
(አሃሃሃሃሃ) ያለህበት ችግር ግልጽ ሆኖ ታየኝ
(አሃሃሃሃሃ) ለዚህማ አምልኮ ምሥጋና ነው መልሱ
(አሃሃሃሃሃ) አሁን ተነሳልህ ኢየሱስ ንጉሡ
ወደቀልህ ሰንሰለቱ በኢየሱስ በክንደ ብርቱ
ወደቀልህ በሽታው ለዘላለም እንዳታየዉ
መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይለኛል
እንዲህ ይለኛል እንዲህ ይለኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
ገና (፫x) ገና ነው
ገና (፫x) ነው
ገና ነው የአባቴ ስራ
ገና ነው በእኔ የጀመረው
ገና ነው መቼ ተፈጸመ
ገና ነው ማነው ቆሟል ያለ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ