የእኔማ
Yeniema
2015 · ትራክ 1 · 6:40 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የእኔማ ፣ የእኔማ ሰላም የእኔማ
የእኔማ ፣ የእኔማ ደስታ የእኔማ (፪x)
ከዚህ ዓለም አይደለም በመንፈሱ ነው
በብርም በወርቅም የማይገዛው
በወንጌል ሞኝነት በአመንኩት ቃል
ሰላሙ ከሆዴ ይፍለቀለቃል
አገዘኝ አገዘኝ (፰x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠላቴ ዓይኑ እያየ
በመንፈሱ ነካኝ አትረፈረፈኝ
አገር ምድሩ እያየ
በቅባቱ ነካኝ አትረፈረፈኝ
አገዘኝ አገዘኝ (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (አሄ)
ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (፪x)
ይውጣ ወደላይ ከድንኳኔ
የአምልኮ የዝማሬው ቅኔ
የሆንክልኝን ሳስበው
ከዚህ በላይ ምን አለ ምሆነው
ከፍ በልልኝ (፬x)
ደምቀህ ታይልኝ (፬x)
ና ሲለኝ ቃሉን ተማምኖ በውኃው ላይ
ና ሲለኝ እጁ እንደማይጥል አታዩም ወይ
ና ሲለኝ ከሁኔታ ጋር እርሱ አይለካ
ና ሲለኝ መንገድ ይሆናል ውኃውም ለካ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላቴ ዓይኑ እያየ
በመንፈሱ ነካኝ አትረፈረፈኝ
አገር ምድሩ እያየ
በእሳቱ ነካኝ አትረፈረፈኝ
አገዘኝ አገዘኝ (፰x)
አዝማች · Chorus
የእኔማ የእኔማ ሰላም የእኔማ
የእኔማ የእኔማ ደስታ የእኔማ (፪x)
ከዚህ ዓለም አይደለም በመንፈሱ ነው
በብርም በወርቅም የማይገዛው
በወንጌል ሞኝነት በአመንኩት ቃል
ሰላሙ ከሆዴ ይፍለቀለቃል
አገዘኝ አገዘኝ (፰x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (አሄ)
ላምልክህ ደግሜ እስኪ ደግሜ ደጋግሜ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ይውጣ ወደላይ ከድንኳኔ
የአምልኮ የዝማሬው ቅኔ
የሆንክልኝን ሳስበው
ከዚህ በላይ ምን አለ ምሆነው
ከፍ በልልኝ (፬x)
ደምቀህ ታይልኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ