Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወደፊት

Wedefit

2015 · ትራክ 3 · 6:32 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልተውም አልተውም አልተውም አምልኮ

በዋጋ የገዛኝ የኢየሱስ ነኝ እኮ

አልተውም አልተውም አልተውም ዝማሬ

ይኸው አልበረደም ውስጤ እስከዛሬ

ወደፊት ነው ወደፊት ወደፊት (፬x)

(አሃሃሃሃሃ) እየተውኩ (አሃሃሃሃሃ) ኋላዬን

(አሃሃሃሃሃ) ለማያዝ (አሃሃሃሃሃ) የፊቴን

ወደፊት ነው ወደፊት ወደፊት (፪x)

ከከበበኝ በላይ በላይ ከችግሬ በላይ

ከጉዳዬ በላይ በላይ

ከጠላቴ በላይ በላይ ከጭንቀቱ በላይ

ከበሽታው በላይ በላይ

ይፈውሳል እጁ

ይፈውሳል እጁ

ሰው ያደርጋል እጁ

ሰው ያደርጋል እጁ (፪x)

ይሄ የማነው የማን እጅ (፫x)

አዋጅ የሚሽር በአዋጅ

ይሄ የማን ነው የማን ስራ (፫x)

በምድረ በዳ አሄ የሚመራ

ገባኝ ገባኝ ገባኝ (፪x)

የጌታ ነው የጌታ (፬x)

የጌታ ነው የጌታ (፬x)

እውነት እውነት እውነቴን ነው

የምዘምረው ከልቤ ነው

የተስፋን ቃል በሰጠኝ

ያ ድቅድቅ ጨለማ ነጋልኝ

ነጋልኝ ነጋልኝ ነጋ (፬x)

በጌታ ነው በጌታ (፬x)

አልተውም አልተውም አልተውም አምልኮ

በዋጋ የገዛኝ የኢየሱስ ነኝ እኮ

አልተውም አልተውም አልተውም ዝማሬ

ይኸው አልበረደም ውስጤ እስከዛሬ

ወደፊት ነው ወደፊት ወደፊት (፬x)

(አሃሃሃሃሃ) እየተውኩ (አሃሃሃሃሃ) ኋላየን

(አሃሃሃሃሃ) ለማያዝ (አሃሃሃሃሃ) የፊቴን

ወደፊት ነው ወደፊት ወደፊት (፪x)

ከከበበኝ በላይ በላይ ከችግሬ በላይ

ከጉዳዬ በላይ በላይ

ከጠላቴ በላይ በላይ ከጭንቀቱ በላይ

ከበሽታው በላይ በላይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ