በድብብቆሽ ቀኑ እንዳያልፍ
Bedebebeqosh Qenu Endayalf
2013 · ትራክ 6 · 6:04 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰርግና ምላሹ ድግሱ ቀለጠ
ከትላንቱ አጀብ የዛሬው በለጠ
የፍቅር ጨዋታው ከመቼው አለቀ
የፍቺ ጥያቄ ፍርድ ቤት ዘለቀ
ጭብጨባው መልካም ነው ዕልልታም ባልከፋ
አዝማች · Chorus
አስቸገረን እንጂ አንገት እያስደፋ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ትዳር ይከበር ቃልኪዳን ይጽና
በመካከሉ አምላክ አለና
መፋታትን እጠላለሁ ብሏልና
ስብከት ሙያ ሆኖ ወንጌልም ለእንጀራ
መዝሙሯ ጸሎቷም . (1) . ተቸርችራ
ቁጥር 3 · Verse 3
ገበያው ቀለጠ ቤተመቅደስ ደጃፍ
ጌታ ተመልሶ እስኪያነሳ ጅራፍ
ምን ትጠብቃለህ ሰብስብ ኮተትህን
አዝማች · Chorus
ያሸጥሃል ኋላ በኩርነትህን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ወንጌል ይሰበክ በእውነት በጽድቅ
በድብብቆሽ ቀኑ እንዳያልቅ
መክሊት ሰጪ አለ ጌታ ሚጠይቅ
ወንድሞች ተጣሉ በመሪነት ሰበብ
ያውም በመድረኩ ጉድ እን
ሽማግሌም ልግዛ መጋቢው ልንገሥ
በኧረኞች ትግል መንጋ ሲታመስ
በብዕር በቃላት ጦፈ ክርክሩ
አዝማች · Chorus
እስቲ መልሱልኝ የማነው ወንበሩ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
መንጋው የኢየሱስ የሞተለት
የበረቱን ቁልፍ አስረክቡት
የእኛ ጥሪ ዝቅታ ነው ሎሌነት
ነጭ ጥቁር ቀለም መለየት አቅቶት
ድንበር የጣሰ ይላል ምናለበት
ጽድቅ ከአመጽ ጋር ብርሃን ከጨለማ
አምላክ ያጣላውን ማን አለህ አስማማ
ይልቅ ከዓለም ተለይ ውጣ ተቀደስ
አዝማች · Chorus
የትም እየረገጥክ ቤቱን አታርክስ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እልፍ በል ውጣ ተለይ
ስሙ ተጠርቷል በአንተ ላይ
የሚመጣ ሙሽራ አለህ ከሠማይ
ሆድም ለመብል ነው መብልም ለሆድ
ሁሉም ይጠፋሉ ብንወድም ባንወድ
አንዳንዴም በመጾም ጐሽም ሥጋህን
አብልቶ ከሚዘርፍ አስጥል ፀጋህን
እንቅልፍም አይብዛ አርግለት ገደብ
አዝማች · Chorus
ጸሎት አይረሳ ቃሉም ይነበብ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ተነስ ተጋደል ጸንተህ ተዋጋ
ያበረታሃል የአምላክህ ፀጋ
የትም መቼም ጌታ እንዳለ አትዘንጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ