Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድረስልኝ

Dereselegn

2013 · ትራክ 7 · 7:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በጉድለት ነው የምመላለሰው

የሞላሁኝ እመስላለሁ ለሰው

ያውቀው የለ ጌታ ውስጤን ዘልቆ

ግብዝነት የትም አይሄድ ርቆ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ቀባብቼ ውጬዬን አሳምሬ

ማስመሰሉን እንጃ ከየት ተምሬ

መቅረብ ትቼ ሆኜ እራሴን

አዘገየው መጐብኘት ፈውሴን

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

አውቀዋለሁ ባሕረ ገሊላ

አይካድም አሳም እንደሞላ

የማጥመድስ ልምድ መች አጥቼ

ልሂድ እንጂ ዋናውን ረስቼ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ወደ አንተ እገሰግሳለሁ

ለረድኤት እጄን አነሳለሁ

ኧረ ወዴት ወዴት ሊኬድ ከቶ

የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ አንተን ትቶ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ይህ አየነ ስውር ደግመህ ብትዳስሰው

አጥርቶ አየ ለይቶ ዛፍ ከሰው

ደግመህ ዳሰኝ እኔንም ጌታዬ

እልፍ ይበል ይስፋ እይታዬ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅልን እባክህ

ጠጥተንህ እንድንባረክ

ለልጆችህ ላለን በበረሃ

ፍሰስልን አንተ የሕይወት ውሃ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ድረስልኝ (፬x) ምርኮዬን መልስልኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ