ሌላ ነገር ይቅር
Liela Neger Yeqer
2013 · ትራክ 3 · 5:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሌላ ነገር ይቅር ይወራ ስለ እርሱ
በከበረው ደሙ ኃጢአት መደምሰሱ (፪x)
አንተ አንቺ: ሳይባል ሁሉም ሰው ይመነው
ኢየሱስን ማጣት ሁሉንም ማጣት ነው (፪x)
የባህል እስራት የኃጢአት ቁራኛ
እስከመቼ ድረስ እያለን መዳኛ
ፍርድና ኩነኔ ለከደነው ሁሉ
መቃብርን ከፋች ኢየሱስ አለ በሉ
አዝማች · Chorus
ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት
ቁጥር 2 · Verse 2
የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ቃሉን ስለናቀ
በአዳም መተላለፍ ሁሉም ሰው ወደቀ (፪x)
የዓለምን ኃጢአት በእንጨት ሊሸከም
ሥጋ ለብሶ መጣ ሁለተኛው አዳም (፪x)
ምርኮኛን የሚያስለቅቅ እስራት የሚያስፈታ
ምህረትን ይዞ የመጣውን ጌታ
አምኖ ይቀበለው የሰው ዘር በሙሉ
ኢየሱስ ያድናል የምስራች በሉ
አዝማች · Chorus
ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰይጣኔ አገዛዝ ቀንበሩን ሲያከብድ
የዓለም እንቆቅልሽ እየበዛ ሲሄድ (፪x)
ኃያላን ነገሥታት ፈላስፎች ቢሆኑ
ሊያድን የተቻለው ማነው ለመሆኑ (፪x)
የመዳንን እራስ በመስቀል ፈጽሞ
ቤት ሊያዘጋጅልን የሄደልን ቀድሞ
በሕያዋን በሙታን ሊፈርድ የሚመጣው
የጽዮን ሙሽራ ጌታ ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ