በምሥጋና ሁሉ ላይ
Bemesgana Hulu Lay
2013 · ትራክ 11 · 7:23 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቅዱሳን መላዕክት ሱራፌል በሠማይ ያሉ
ሳያቋርጡ ዘወትር ለአንተ ይሰግዳሉ
ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ቁጥር የሌላቸው
በቀን በማታ እንዲያበሩ የፈጠርካቸው
የጥበብህ ስራ ምሳሌ ናቸው
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ደማናዎችህ እንደጥጥ የተባዘቱ
ማሰሮው ሲያዘነብል በልጉ ክረምቱ
የሠማይ አዕዋፍ በየዘር በየወገኑ
ማን ይናገራል የዕውቀትህ ልኩ መጠኑ
በየቋንቋቸው ሲያመሰግኑህ
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የምድር ፍጥረታት ሕያዋን ተንቀሳቃሾች
ሰዎች እንስሳት አራዊት የባሕር አሶች
ውቅያኖስ ወንዙ ሸለቆው ደኑ ተራራ
አቤት ሲያስደንቅ የቃልህ የእጅህ ስራ
ሁሉም በቋንቋው ክብርህን ያውራ
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በዓለም ታሪክ በዘመን በአመታት መሃል
የሌለህበት ያለአንተስ የሆነ የታል
ነገሥታት ሲያልፉ ኃያላን ወድቀው ሲቀሩ
ድንቅ የተባሉ ግኝቶች ሲያልፉ ሲሻሩ
የእኛ እግዚአብሔር አለ በክብሩ
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አቤቱ ስራህ አሳብህ ሁሉም ድንቅ ነው
ከዚህ ሁሉ በላይ ሚይስደንቅ መዳናችን ነው
በመጀመሪያ በአንተ ዘንድ የነበረው ቃል
በድንግል ማህጸን ሰው ሆኖ መድን ተወልዷል
ጨካኙን ዘንዱ በመስቀል ራሱን ቀጥቅጦ
አመተ ፍዳን በአመተ ምህረት ለውጦ
ሁሉን ድል አድርጐ በቀኝህ ለተቀመጠው
በክብር በሥልጣን ዳግመኛ ለሚገለጠው
ክብር ምሥጋና ውዳሴ ይኸው
አዝማች · Chorus
በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ (፫x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ይባረክ ይባረክ ፤ ይባረክ ይባረክ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ