ክብር ለክብር ጌታ
Keber Lekeber Geta
2013 · ትራክ 5 · 6:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ክብር ለክብር ጌታ
ውዳሴና ዕልልታ
አምልኮና ስግደት
ኢየሱስ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ይሁንለት (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መላዕክት በሠማይ ያሉ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ
ቀን የላቸው ሌሊት ሁልጊዜ የሚያከብሩት
ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኃያል የክብር ጌታ
መጽሐፉን የከፈተ ማኅተሙን የፈታ
አዝማች · Chorus
ክብር ለክብር ጌታ
ውዳሴና ዕልልታ
አምልኮና ስግደት
ኢየሱስ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ይሁንለት (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የወደቁ መላዕክት አጋንንት በጥልቅ ያሉ
ስሙ ሲጠራባቸው ሁሌ ይንቀጠቀጣሉ
ተራሮች ሚጤሱለት ኮረብቶች ሚዘሉለት
ጌታ የጌቶች ጌታ ኢየሱስ የጽዮኑ ዓለም
አዝማች · Chorus
ክብር ለክብር ጌታ
ውዳሴና ዕልልታ
አምልኮና ስግደት
ኢየሱስ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ይሁንለት (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍጥረት መጀመሪያ ከሙታንም በኩር
ሁሉ በእርሱ የሆነ ኢየሱስ ቃለ እግዚአብሔር
ፀጋ እውነትን ተሞልቶ በእኛ ዘንድ ያደረ
ክርስቶስ አልፋ ኦሜጋ ያለና የነበረ
አዝማች · Chorus
ክብር ለክብር ጌታ
ውዳሴና ዕልልታ
አምልኮና ስግደት
ኢየሱስ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ይሁንለት (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከዘር ከነገድ ሁሉ ከአገር ከወገን
እኛን በደሙ አጭቶ ካህናት ያደረገን
መንፈሱን ያፈሰሰ ፀጋውን የሰጠን
የናዝሬቱ ኢየሱስ ክብር ለእርሱ ይሁን
አዝማች · Chorus
ክብር ለክብር ጌታ
ውዳሴና ዕልልታ
አምልኮና ስግደት
ኢየሱስ ይሁንለት (፪x)
ኢየሱስ ይሁንለት (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ