አቀበት ሜዳ
Aqebet Meda
2013 · ትራክ 9 · 4:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቀበት ሜዳ ገደላ ገደል
የታለፈበት የሚረሳ አይደል
ነዳፊው እባብ ነካሹ አውሬ
ስንት አስረገጠኝ በዚህ በእግሬ
የሠማይ አምላክ አቤት ምህረቱ
ማድረግ ይችላል ደካማን ብርቱ
በእርሱ ሆናችሁ ያያችሁ ብዙ
በዕልልታ ሆታ ምሥጋናን አብዙ
አዝማች · Chorus
ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ
መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ
የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ
ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ
ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ
ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ
የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ
ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ይሄ ክፉ ዓለም ምኑ ይመቻል
በሥጋ በደም የትኛው ሲቻል
በየማለዳው አዲስ በሆነው
በምህረቱ ነው ያልጠፋነው
እንደ እኔ ቢሆን እንደድካሜ
ዛሬም በፊቱ ባልታየሁ ቆሜ
በዓይኔ እያየሁት አለፈ ስንቱ
የያዘኝ አምላክ እግዚአብሔር ብርቱ
አዝማች · Chorus
ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ
መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ
የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ
ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ
ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ
ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ
የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ
ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ይህን ዮርዳኖስን ስሻገረው
ደረቅ በትር ነው በእጄ የነበረው
ዛሬ ግን ይሄው ዓለመለኝ
በተዓምራቱ እያስገረመኝ
ሕይወት ዥንጉርጉር ቀለሙ ብዙ
መች ቀላል ሆነ ጓዙ መዘዙ
የሰበሰበኝ የያዘኝ ጌታ
ስሙ ከፍ ይበል በዕልልታ ሆታ
አዝማች · Chorus
ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ
መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ
የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ
ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ
ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ
ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ
የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ
ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ