እስከ ዛሬ የጠበቀኝ
Eske Zarie Yetebeqegn
2013 · ትራክ 8 · 8:04 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስከዛሬ የጠበቀኝ በእጁ ይዞ ያለቀቀኝ
የክርስትናን ቀጭን መንገድ የሕይወትን ውጣ ውረድ
ባይበዛልኝ የእርሱ ፀጋ አንዷም ሌሊት አትነጋ
ዛሬም ቆምኩኝ በዚህ ቦታ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደጠላት አሳብ ቢሆን ከሆነልኝ አንዱም አይሆን
ታሪክ ቢያብብ ሕይወት ቢያምር ሁሉም ነገር በእርሱ ተዐምር
ከእያንዳንዷ እስትንፋስ ስጦታ ናት የኢየሱስ
ከፈቀደ ይሁን ካለ አይሆንም የሚል ማን አለ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ጠላቴ ቀናተኛ መቼም ቢሆን አትተኛ
እንደተራበ አንበሳ ዙሪያዬን ብትዞር እያገሳህ
ልትውጠኝ ብትመኘኝ ሲያምርህ ይቅር አታገኘኝ
በስሙ አጥር በደሙ እሳት ከልሎኛል የእኔ አባት (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና
ቁጥር 4 · Verse 4
ያንን ዘንዶ እባቡን የወጋኸው ወገቡን
ራስ እራሱን ያስረገጥከኝ ስንቱን ነገር ያስመለጥከኝ
ኢየሱስ የእኔ ጋሻዬ በክፉ ቀን መሸሺያዬ
መቆሚያዬ ነህ አለቴ ላመስግንህ በአንደበቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ