በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል
Beferesew Qeter Man Yeqomal
2007 · ትራክ 9 · 5:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የእግዚአብሔር ቤት ፈርሶ
መሠዊያው ተድበስብሶ
የእራስህን ቤት ትሰራለህ
ስለ ወንጌል አይገድህ
በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል
ሁሉ የራሱን ድንጋይ ይክባል
በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል
ኤሎሂ ማን ይሻለናል?
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ
ስለ ቤትህ የሚሳሳ
ግድ የሚለው የወንጌል ነገር
በጥቅም የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፫x) አሃ ኤሎሂ
ቁጥር 3 · Verse 3
የቀደሙት ሃዋሪያት ነቢያት
ራሳቸውን ሰጡ እስከሞት ድረስ
ዛሬ ራሱን ሚሰጥ ኧረ እርሱ ማነው
የወንጌሉ ቅናት ውስጡን የበላው
እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ
ስለ ቤትህ የሚሳሳ
ግድ የሚለው የወንጌል ነገር
በጥቅም የማይጭበረበር
ቁጥር 4 · Verse 4
ወንድም ለወንድሙ ማዘን ሲገባዉ
ባደባባይ ላይ ክስ ዝንተላዉ ምንድን ነው
እውነቱ ከተቀየረማ ከቀለላ ዋጋው ክርስትና
ምንድን ነው የሚሻለን ኤሎሂ መፍትሄ ስጠን
እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ
ስለ ወንድሙ የሚሳሳ
ግድ የሚለው የፍቅር ነገር
በውሸት የማይወነጅል
አዝማች · Chorus
ኤሎሂ (፫x) አሃ ኤሎሂ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትውልድ ሲተራመስ በራሱ መንገድ ላይ
ግማሹ ወደታች ግማሹ ወደላይ
ወዴት እንደምሄድ ትውልድ አላወቀም
የዛሬን እንጂ የነገን አላየም (፪x)
እግዚአብሔር ሆይ ሰው አስነሳልን
መንገድህን የሚያሳየን
ቃልህን ብቻ የሚናገር
በሁኔታ የማይጭበረበር
ቁጥር 6 · Verse 6
ኤሎሂ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
የቀደሙት ሃዋሪያት ነቢያት
ራሳቸውን ሰጡ እስከሞት ድረስ
ዛሬ ራሱን ሚሰጥ ኧረ እርሱ ማነው
የወንጌሉ ቅናት ውስጡን የበላው
እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ
ስለ ቤትህ የሚሳሳ
ግድ የሚለው የወንጌል ነገር
በጥቅም የማይጭበረበር
ቁጥር 8 · Verse 8
እግዚአብሔር ሆይ ሰው አስነሳልን
መንገድህን የሚያሳየን
ቃልህን ብቻ የሚናገር
በሁኔታ የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፬x)
ቁጥር 9 · Verse 9
የእግዚአብሔር ቤት ፈርሶ ፣ መሠዊያው ተድበስብሶ
የእራስህን ቤት ትሰራለህ ፣ ስለ ወንጌል አይገድህ
በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል
ሁሉ የራሱን ድንጋይ ይክባል
በፈረሰው ቅጥር ማን ይቆማል
ኤሎሂ ማን ይሻለናል?
እግዚአብሔር ወይ ትውልድ አስነሳ
ስለ ቤትህ የሚሳሳ
ግድ የሚለው የወንጌል ነገር
በጥቅም የማይጭበረበር
አዝማች · Chorus
ኤሎሂ (፫x) አሃ ኤሎሂ
ቁጥር 10 · Verse 10
ኤሎሂ (፫x) አሃ ኤሎሂ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ