ጌታዬ ጌታዬ
Gietayie Gietayie
2007 · ትራክ 13 · 5:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብቻዬን ቁጭ ብዬ አዝኜ በቤቴ
በጣም እያመመኝ ይሄው ስብራቴ
በድንገት ኢየሱስ ደረሰልኝ
ሰባራውን ጠጋኝ እውነተኛ ዳኛ
የደካሞች አሳራፊ
ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ
ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ
ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ
ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ
ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
የፈተና መዓት በላዬ ቢፈስ
ፀሎቴም በሙሉ ባይመለስ
ዝቅ ዝቅ እላለሁ ሌላ አያምረኝም
ቤዛዬን ኢየሱስ በፍፁም አልክድም (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃጢአተኛ ሳለሁ ሰዎች ሲገፉኝ
የናዝሬቱ ኢየሱስ አይቶ ራራልኝ
እንደ ኃጢአቴ ያልፈረደብኝ
የእግዚአብሔር ልጅ እርሱ ለእኔ አዘነልኝ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ኢየሱስ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
የደካሞች አሳራፊ
ኢየሱስ አለ ነፍሴ እረፊ
ሸክም ከብዶበት የሚንገላታ
ወደዚህ ጌታ መጥቶ ይበርታ
ዓይኔን አንስቼ ከሰው ላይ
ሀዘኔን ረሳሁ ኢየሱስን ሳይ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ጌታዬ ከሞት መዳኛዬ
ኢየሱስ ጌታዬ የዓይኔ ማረፊያዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ