ቃል አለኝ
Qal Alegn
2007 · ትራክ 6 · 4:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፈውሱን ፍልጌ ስንከራተት
መፍትሄ አጥቼ ስባትት
አንዴ ወደዛ አንዴ ወዲህ ስል
እሩጬ ሩጬ ልቤ እስኪዝል
ከዚህ ሁሉ ጣጣ የገላገለኝ
የዳዊት ዘር ነው ቃልን የሰጠኝ
በአንዲት ቃል ብቻ ተገላገልኩ
ተባረክ ብዬ አመሰገንኩ
አዝማች · Chorus
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (፪x)
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ
(ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ
(ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ
(ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ
(ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ (፭x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከጨለማ ውስጥ እኔን የጠራኝ
አስደናቂውን ብርሃን ያሳየኝ
የተናኩትን ና ብሎ ጠርቶ
በወንጌል ዘይት ራሴን ቀብቶ
የሚያየኝ ሁሉ እስኪገረም
አቆመኝ ጌታ ለምስክር
እንደ መልካሙ እንደዛ መሬት
ቃሉን ዘራብኝ አረኩኝ ሀሴት
አዝማች · Chorus
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (፪x)
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ
(ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ
(ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ
(ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ
(ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደ አብርሃም በድንቅ የጠራኝ
ሁሉንም ተወው ውጣ አትፍራ ያለኝ
እስከ ዓለም ፍጻሜ ከእኔ ጋራ ነው
የቃሉ መንፈስ በውስጤን ያለው
ስለዚህ አልፈራም አልሸበር
ድምፅን ሰማሁኝ ከእግዚአብሔር
ወድቄ የምቀር መቼ ሆንኩና
ጌታ ነግሮኛል ሄዳልሁ ገና
አዝማች · Chorus
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ (፪x)
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ
(ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ
(ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ
(ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ
(ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ (፭x)
ቁጥር 4 · Verse 4
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ
(ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ
(ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ
(ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ
(ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ