ፀጋው ነው
Tsegaw New
2007 · ትራክ 10 · 5:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ
ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁልጊዜ ችኩል ነው ሲያዩት ደፋር መሳይ
ዶሮ ሳይጮህ በፊት ሶስት ጊዜ ክህዶታል
በሰው አይን ቢሆን ይህ ሰው ከሀዲ ነው
የፀጋው ጉልበት ግን ዳግም ሰው አረገው
አዝማች · Chorus
ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ
ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቢሆንማ ኑሮ በክብር በዝና
በገንዘብም ብዛት ብዙ ብልጥግና
እንዴት እሆን ነበር እርቆኝ መዳኔ
ግን እንዲያው ወደደኝ አሰበኝ መድህኔ
እንደ ሰው አይደለም ጌታዬ ልዩ ነው
የተረሳውን ሰው እንዲህ ሚያስታውሰው
አዝማች · Chorus
ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ
ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በማይመስል ነገር መስራት የሚችል
የአለምንም ጥበብ በኔ ሚያሳፍር
ልጁንም ገለጠው በእኔው ሁኔታ
እኔን ውዳቂውን አከበረ ጌታ
አዝማች · Chorus
ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ
ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በራሴ አልቆምኩም ሚስጥሩ ገብቶኛል
ጸጋን አትረፍርፎ እየሱስ ሰጥቶኛል
ከቶ ዝም አልልም አዜምለታለሁ
ላከበረኝ ጌታ ክብር እሰጣለሁ
እንደ ሰው አይደለም ጌታዬ ልዩ ነው
የተረሳውን ሰው እንዲህ ሚያስታውሰው
አዝማች · Chorus
ፀጋው ነው እኔን የሚያቆመኝ
ምህረቱ ነው እንዲህ የሚያዘምረኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ