እግዚአብሔር መልካም ነው
Egziabhier Melkam New
2007 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሕይወቴ ያለፈውን ዞር ብይ ሳየው ስመለከተው
የእኔ ጉልበት ሳይሆን እዚህ ያደረሰኝ መልካምነቱ ነው
የእኔ ብርታት ሳይሆን እዚህ ያደረሰኝ ኧረ እርሱ ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ነው (፪x)
የሚመስለው ማነው
በመልካምነቱ በመልካምነቱ ታጋሽ ርህሩህነቱ
ነገሬ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፪x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የእራሴ አስተዋፅዖ አንድም የሌለበት
ያልደከምኩበት እዚህ ለመድረሴ
ምክንያቱ አንድ ነው እግዚአብሄር መልካም ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ነው (፪x)
የሚመስለው ማነው
በመልካምነቱ በመልካምነቱ ታጋሽ ርህሩህነቱ
ነገሬ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፪x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በምድረ በዳ ላይ አንድ ነገር ሳይኖር
ምንጭን አፈለቀ ጌታ በተዓምር
የምድረ በዳዉ ሃሩር ሳያገኘኝ
የነ ሙሴ አምላክ ተጠነቀቀልኝ
ወጥመድ ተሰበረ ወጥመድ ተሰበረ
ጌትዬ ከበረ
ወጥመዱን ሲሰብረው ወጥመዱን ሲሰብረው
ባይኔ አይቻለሁ
በሕይወቴ ያለፈውን ዞር ብይ ሳየው ስመለከተው
የእኔ ጉልበት ሳይሆን እዚህ ያደረሰኝ መልካምነቱ ነው
የእኔ ብርታት ሳይሆን እዚህ ያደረሰኝ ኧረ እሱ ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ነው (፪x)
የሚመስለው ማነው
በመልካምነቱ በመልካምነቱ ታጋሽ ርህሩህነቱ
ነገሬ የሰመረው (፫x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፪x)
ከኢየሱስ የተነሳ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ