ሊቀ ካህኔ
Liqe Kahenie
2007 · ትራክ 3 · 5:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስደክም የሚያበረታኝ
በውድቀቴ የማይስቅብኝ
በፍቅር ዓይኖቹ የሚያየኝ
ደጉ ሊቀ ካህን አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሊቀ ካህኔ ኢየሱሴ (፪x)
ጠበቃዬ ኢየሱሴ
አለልኝ በሰማይ ለነፍሴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ታማኙ የነፍሴ ጠባቂ
ኢየሱስ ለእኔ አዋቂ
ዳኛዬ ቅኑ ፈራጄ
ኢየሱስ እርሱስ ወዳጄ
የልጅነት አባት የሆነኝ
እንዳልወድቅ የቆመልኝ
ካህኔ ጠባቂ የነፍሴ
ይገባሃል አምልኮ ውዳሴ
የልጅነት አባት የሆነኝ
እንዳልወድቅ የቆመልኝ
ካህኔ የነፍሴ ጠባቂ
ኢየሱስ ለእኔ አዋቂ
ታማኙ የነፍሴ ጠባቂ
ኢየሱስ ለእኔ አዋቂ
ዳኛዬ ቅኑ ፈራጄ
ኢየሱስ እርሱስ ወዳጄ
ጉድ አሉ የሚያውቁኝ በሙሉ
በመቆሜ ሁሉም ተገረሙ
እኔ ግን እንደዚህ እላለሁ
መቆሜ ከእርሱ የተነሳ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሊቀ ካህኔ ኢየሱሴ (፪x)
ጠበቃዬ ኢየሱሴ
አለልኝ በሰማይ ለነፍሴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ