በታምራት
Betamerat
2007 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔ ቀኑ ጨልሞ መስማት እንጂ ማየት አልችል
ጥዋት ልለምን የወጣሁ መሽቶ በሰው ነው ምገባው
ትንሽ ትልቅ መሪዬ የሰው ፍቃድ ማደሪያዬ
የእድሜዬን ግማሽ ቆጠርኩ ጨለማውን ለመድኩ
አዝማች · Chorus
መጣ ኢየሱስ
ይሄ የአለም ብርሃን
ዓይኖቼን ከፈተ በእውርነቴ ሃገር
ታሪኬ ተለወጠ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተከፈተ ብርሃኔ
መልካምነቱን አየሁት በዚህች በአጭሯ ዘመኔ
ተጥዬ የነበርኩ ያምስኪኑ እኔ ነኝ
መንገደኛ የማያየኝ አሳዛኝ ሰው ነበርኩኝ
በሀጥያቱ ወደቀ በእግዚአብሔር ደቀቀ
ብለው ሰዎች ፈርዱ ስብራቴን ሳይረዱ
አዝማች · Chorus
ደጉ ጌታ ከሰማይ አየኝ
ከውድቀቴ አነሳኝ ቁስሌን ፈውሶ
አከበረኝ መልሶ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በታምራት የሚያኖረኝ አምላክ አለኝ የሚያስብልኝ
የመቆሜ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ምህረቱ
ባልጋዬ ላይ ተኝቼ ለአመታት ሸትቼ
መልዐኩ ሲያናውጠው ማን ሊከተኝ ወደ ውሃው
ዘመድ አዝማድ የለኝ እኔ የምለው ሚረዳኝ
ቀርቦ ችግሬን አየና ተራመድ ሂድ ተነሳና
ያለው ጌታ ለካ ዘመዴ ነው ስለ እኔ የሚሰማው
አዝማች · Chorus
ሽባነቴን ሽሮ አቆመኝ ቀይሮ (፪x)
በታምራት የሚያኖረኝ አምላክ አለኝ የሚያስብልኝ
የመቆሜ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ምህረቱ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ