በፍፁም ልባቸው እንዲያገለግሉት
Befetsum Lebachew Endiyagelegelut
ትራክ 10 · 3:22 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በፍፁም ልባቸው እንዲያገለግሉት
በእርሱና ለእርሱ ደግሞ እንዲኖሩለት
ጌታ ልጆቹን ያጠራል ከኃጢአት ያነጻቸዋል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በእንሰሳት ፋንድያ ቤቱ እንደዚያ ገምቶ
ያን የጥንቱን ጠረን መዓዛውን አጥቶ
ኢየሱስ አያስችለውም ሳያነጻ አያልፈውም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከቤተ-መቅደስ ውስጥ ሸቀጡን አራግፎ
የሚቸረችረውን ነጋዴውን ገርፎ
አስወጥቶ ያባርራል ቅንአቱ ያቃጥለዋል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አብሮ አደግ እንክርዳድ ስንዴውም ሲታጨድ
አስተዋይ ገበሬ ያንን መንሹን ሲሰድ
ምርቱን ከግርዱ ይለያል ፣ ገለባውን ለእሳት ይሰጣል (፪x)
አዝማች · Chorus
በፍፁም ልባቸው እንዲያገለግሉት
በእርሱና ለእርሱ ደግሞ እንዲኖሩለት
ጌታ ልጆቹን ያጠራል ከኃጢአት ያነጻቸዋል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ