አዲስ ዝማሬ እንዘምር
Addis Zemarie Enzemer
ትራክ 4 · 4:15 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አዲስ ዝማሬን እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በዕልልታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በእረኛቸው የታመኑ ፣ በመስኩ የተሰማሩ
ዱካውን እየተከተሉ ፣ ለደህንነት የተጠሩ
ከጨካኝ አውሬ የዳኑ ፣ ከመታረድ የተረፉ
ሃሴትን እንደሚያደርጉ በአጥፊው ጥፋት ስላልጠፉ
አዝማች · Chorus
አዲስ ዝማሬን እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በዕልልታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማቃችንን ቀዷልና ፀጋውን አልብሶናልና
ክብራችን ትዘምርለት ፍቅሩ አጽናንቶናልና
ጉዳታችንን የሚሹ ጉድጓድ ምሰው የጠበቁን
አጋንንት አፍረዋልና ያደፈጡት ሊያጠቁን
አዝማች · Chorus
አዲስ ዝማሬን እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በዕልልታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍፁም ልብ እንዘምር ፣ በአምላካችን ደስ ይበለን
እናጨብጭብ ዕልል እንበል ፣ ለምንስ እንቆጥባለን
በምሥጋናችን ዝማሬ ምሽጉን እናፈርሳለን
በመንፈሳዊው ጦር ዕቃ ድል በድል እንሄዳለን
አዝማች · Chorus
አዲስ ዝማሬን እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በዕልልታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ