ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
Tebib Betebebu Aymeka
ትራክ 3 · 3:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አመጻዬ ወደ ምድረ በዳ ወሰደችኝ
ውኃ በሌለው በረሃ አንከራተተችኝ
ለውድቀቴ እውቀት ትዕቢትን አስተማረችኝ
ጥማት ሲያቃጥለኝ ፣ እልህ ሲታገለኝ
እውነት ስትወርሰኝ ፣ ጥበብ ስትገስጸኝ
መንፈሱ ሲረታኝ ፣ ጌታን አገነሁት
አዝማች · Chorus
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
ኃያልም በኃይሉ አይመካ
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን
በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ
በጌታ ይመካ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰማያዊ ጥበብ ዓይንን ትከፍታለች
ለሰነፎች ብልሃትን ታስተምራለች
ከምዝምዝ ወርቅና ከቀይ ዕንቁ ትበልጣለች
አጥብቀህ ብትሻት ብትፈላልጋት
ድምጽህን አንስተህ ጥበብን ብጠራት
ያን ጊዜ ታውቃለህ እግዚአብሔርን መፍራት
አዝማች · Chorus
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
ኃያልም በኃይሉ አይመካ
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን
በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ
በጌታ ይመካ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የዚህች ዓለም መርማሪ ወዴት አለ
የዘመናትን ጥያቄ ያቃለለ
ኢየሱስ ነው ሊቁ ለእኛ የተሰቀለ
ከበረሃው መሃል ሕይወት ያፈለቀ
የሰይጣንን ስልጣን መትቶ ያደቀቀ
ለእርሱ ስንሸነፍ ጥያቄው አለቀ
አዝማች · Chorus
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
ኃያልም በኃይሉ አይመካ
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን
በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ
በጌታ ይመካ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ