በእምነት ድል እየነሱ
Bemnet Del Eyenesu
ትራክ 7 · 3:53 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን
የቀደሙትን እያየን ከፊታችን
ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን
የሕይወት ምርጫችን
እርሱ ነውና ዋስትናችን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሁሉ የሚበልጠውን ተመልክተው
ከየምድሩ ጉድጓድ ተቅበዝብዘው
ነፍስን ከሚዋጋ ምኞት ርቀው
ወንዙን ተሻገሩ አሸንፈው (፫x)
አዝማች · Chorus
በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን
የቀደሙትን እያየን ከፊታችን
ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን
የሕይወት ምርጫችን
እርሱ ነውና ዋስትናችን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቅን ከምትመስል ሰፊ መንገድ
ወጥተን በጠባቡ ስንሰደድ
በዚህ ጐዳና ላይ ሕይወት አለ
ቆርጦ ለሚከተል የታደለ (፫x)
አዝማች · Chorus
በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን
የቀደሙትን እያየን ከፊታችን
ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን
የሕይወት ምርጫችን
እርሱ ነውና ዋስትናችን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባለ ፀጋ ሲሆን ደህይቶልን
ባለ ማዕረግ ሲሆን ተዋርዶልን
እውነተኛውን ፍቅር ገለጸልን
እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን (፫x)
አዝማች · Chorus
በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን
የቀደሙትን እያየን ከፊታችን
ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን
የሕይወት ምርጫችን
እርሱ ነውና ዋስትናችን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ