ፈቃድህን እንዳደርግ
Feqadehen Endaderg
ትራክ 11 · 2:56 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልቤን ስፈጽም አምላኬን ሳልፈራ
ለኋለኛው ዘመን ሳከማች መከራ
ኃጢአትን ስዘራ የኖርኩትን ኑሮ
ፀጋህ አሳመረው ሕይወቴን ቀይሮ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ
በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈቃድህን አውቆ መታዘዙ ጠቅሞኝ
ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ሆኖልኝ
መልካም ሥርዓትህን ተምሬ ተምሬ
በእንግድነት ሐገር እዘምራለሁ ዛሬ
አዝማች · Chorus
እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ
በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፈቃድህ ድንቅ ነው የፈጸምከው በእኔ
ለዛሬም ለነገም ባንተ ላይ ነው ዓይኔ
በምሄድበትም መንገዴን አሳየኝ
በቀረልኝ ዘመን ፈቃድህን አስታውቀኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ
በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ