እጁን ዘርግቶ
Ejun Zergeto
ትራክ 2 · 3:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሞትንስ ፍርድ ብዙ ጊዜ ሰምተናል
በሕይወት ለመኖር ዕለት ዕለት ሞተናል
የኢየሱስን ሞት ተሸክመን ዞረናል
በዚህ ሁሉ ግን በምህረቱ ኖረናል
አዝማች · Chorus
እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ
በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ
ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን
ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን
ቁጥር 2 · Verse 2
በእምነት እንጂ በምናየው አይደለም
ከጌታ በቀር እኛ ትምክህት የለንም
ጽድቃችን እንኳን ለዚህ አላበቃንም
ፀጋው አጽንቶን ከርሱ አልተለየንም
አዝማች · Chorus
እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ
በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ
ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን
ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን
ቁጥር 3 · Verse 3
ሕያዋን ሆነን በእርሱ እንኖራለን
የጌታን ሥራ ዛሬም እንገልጻለን
ክብር ለሥሙ ሞገስ ለሥሙ ብለን
ያለንን ሁሉ ለእርሱ እንሰዋለን
አዝማች · Chorus
እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከእኛ ጋር ሆኖ
በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ
ረግረጉ ውጦን ልንጠፋ ነበር ውኃ አስጥሞን
ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ