Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ና ጌታ

Na Gieta

ትራክ 15 · 3:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሕዝብህ ይጠብቅሃል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

መገለጥህ ናፍቆታል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

እባክህ ናልኝ ሳትቆይ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ጊዜው አልደረሰም ወይ ? ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ና ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ! (፫x)

ጊዜው አልደረሰም ወይ?

ስምህን ስለወደደች ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ነፍሴ ስድብን ጠገበች ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታዬ ሆይ!

ባርኮቷን እያሰበች ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ዛሬም በአንተ ታምናለች ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ና ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ! (፫x)

ጊዜው አልደረሰም ወይ?

ድካሙ ሳይበረታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

አርበኛው ሳይረታ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

የተጋዳይ አለኝታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

በጠላትህ ላይ በርታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ና ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ! (፫x)

ጊዜው አልደረሰም ወይ?

ጣኦቱ ተሰባብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ልመልከት ስምህ ከብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ከጥንት እንደታወቅህ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ምድር አንተን ትወቅ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ!

ና ጌታዬ ፣ ጌታ ሆይ! (፫x)

ጊዜው አልደረሰም ወይ?

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ