በማለዳ
Bemaleda
2011 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (፬x)
እንዴት ይታለፋል እያልኩ በእኔ ጉልበት
በምድር መፈጠሬን የተራገምኩበት
ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (፪x)
አንተ ስትመጣ በችግሬ ላይ
ጩኸቴን ሰምተህ ስትወርድ ከላይ
የማይቻለውን ስትችል እያየሁ
ከነፍሴ ዜማ ምሥጋና ኢሄው (፪x)
አዝማች · Chorus
በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም
አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና
ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የአምላኬ ጉብኝት ሁልጊዜ??? ደረሰ
የምስኪኑን ሰው እንባው ታበሰ
ቆሞ አደባባይ ቃኘ በገና
ስሙት ሲዘምር አዲስ ምሥጋና (፪x)
አዝማች · Chorus
በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም
አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና
ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (፬x)
የጨለማው ብርታት የማይነጋ መስሎኝ
የጐኔን እንዳላይ ዙሪያዬን ከልሎኝ
ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (፬x)
አለቀ ብላ ነፍሴ ስትፈራ
የደረስክልኝ ስምህን ስጠራ
ጨለማውን ቀን ቀን ያደረግከው
ከነፍሴ ዜማ ምሥጋና ይሄው (፪x)
አዝማች · Chorus
በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም
አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና
ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ