Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቅዱስ

Qedus

2011 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ክብሩ ሰማያትን ምድርን ሸፍኗል

ለሃያልነቱ ምን ቃላት ይገኛል (፪x)

መልአክት በፊቱ ሳያቋርጡ ቅዱስ ይሉታል

ይህ ቅዱስ ይህ ቅዱስ

በብዙ ክብር በብዙ ፍርሃት ይሰግዱለታል

ይህ ቅዱስ አ ቅዱስ

በሰማይ ሆኖ በዙፋኑ ላይ ሁሉን የረታ

ይህ ቅዱስ አሃ ቅዱስ

የማይለወጥ የማይቀየር የክብር ጌታ

ይህ ቅዱስ አ ቅዱስ አይ ቅዱስ ዘለዓለም

ቅዱስ ቅዱስ ዘለዓለም (፫x)

እንደእግዚአብሔር የለም

ለታረደው በግ ኃይል ክብር ባለጠግነት

ሊቀበልህ ይገባል አምልኮ በረከት (፪x)

ሲሉ መላእክት በታላቅ ዜማ ከሩቅ ይሰማል

ይህ ቅዱስ ይህ ቅዱስ

ፍጥረት በቋንቋው አሜን እያለ ይተባበራል

ይህ ቅዱስ አሃ ቅዱስ

ለሕያው ለሆነው ለነበረ ለአለ ለሚመለሰው

ይህ ቅዱስ አሃ ቅዱስ

አምልኮ ክብር ክብር ምሥጋና ለእርሱ ይድረሰው

ይህ ቅዱስ አሃ ቅዱስ

አይ ቅዱስ ዘላለም

ቅዱስ ቅዱስ ዘላለም (፫x)

እንደእግዚአብሔር የለም

ቅዱስ ቅዱስ ዘላለም (፫x)

እንደእግዚአብሔር የለም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ