Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለእኔስ አለኝ

Lenies Alegn

2011 · ትራክ 12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእኔስ እግዚአብሔር መታመኛዬ (፪x)

ለእኔስ እግዚአብሔር መደገፊያዬ (፪x)

ለእኔስ አምላኬ መታመኛዬ (፪x)

ለእኔስ አምላኬ መደገፊያዬ (፪x)

በአምላኬ ጥላ እተማመናለሁ

በመከራዬ ሲረዳኝ እያየሁ

ወጀብ ቢበዛ ልቤ መች ይፈራል

የአምናው ተዐምራት እምነት ሆኖልኛል (፪x)

ምድር ብትናወጥ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ሰማይ ቢንቀጠቀጥ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ተስፋ የማደርገው ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ክንዱ የማይዝለው ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

በአምላኬ ጥላ እተማመናለሁ

በመከራዬ ሲረዳኝ እያየሁ

ወጀብ ቢበዛ ልቤ መች ይፈራል

የአምናው ተዐምራት እምነት ሆኖልኛል (፪x)

ኑሮ ባይመቸኝ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ውጊያው ባይመቸኝ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ክንዱ የማይዝለው ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ተስፋ የማደርገው ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ለእኔስ እግዚአብሔር መታመኛዬ (፪x)

ለእኔስ እግዚአብሔር መደገፊያዬ (፪x)

ለእኔስ አምላኬ መታመኛዬ (፪x)

ለእኔስ አምላኬ መደገፊያዬ (፪x)

በአምላኬ ጥላ እተማመናለሁ

በመከራዬ ሲረዳኝ እያየሁ

ወጀብ ቢበዛ ልቤ መች ይፈራል

የአምናው ተዐምራት እምነት ሆኖልኛል (፪x)

ደካማ ብመስልም ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ወድቄ ባገግም ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ፈጥኖ የሚረዳኝ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

ኦ ብወድቅ የሚያነሳኝ ለእኔስ አለኝ ጌታ (፪x)

በአምላኬ ጥላ እተማመናለሁ

በመከራዬ ሲረዳኝ እያየሁ

ወጀብ ቢበዛ ልቤ መች ይፈራል

የአምናው ተዐምራት እምነት ሆኖልኛል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ