ፍርዱ የማይጓደል
Ferdu Yemayeguadel
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለአንዱ ሲነጋለት ለአንዱ ሲመሽበት
በጠራራው ፀሐይ ቀን ሲጨልምበት
የሰው ማንነቱ በገንዘብ ሲለካ
ሃያል በጉልበቱ በኃይሉ ሲመካ
በገንዘብ ታፍናለት ስትደበቅ
የታመነ ወድቆ የቀጠፈ ሲደርቅ
የዚህ ዓለም ጉዳይ ፍርድ ጐዶሎ ነው
በዘመኔ ታዘብኩ በዐይኖቼ ይህን አየሁ
አዝማች · Chorus
ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ
ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ
በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ
ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው
እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው
እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ለመበለቷ በቅን ይፈርዳል
የሃዘንተኛውን እንባ ያብሳል
ለተገፋው ሰው ለምስኪን አዛኝ
የተሰበረውን በቃል ጠጋኝ
ይኼ ነው አምላኬ የተመማነኩበት
ይኼ ነው ጌታዬ ልቤን የጣልኩበት (፪x)
ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ይመከር
እውነት ሕይወት መንገድ የለም ከእርሱ በቀር (፪x)
እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው
እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው
አዝማች · Chorus
ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ
ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ
በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ
ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው
እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው
እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ያጣ እያገኘ ያገኘም እያጣ
የወጣም ወረደ የወረደም ወጣ
እንደጊዜው ሆኖ ሕይወት ሲቀያየር
ሃያል ጉልበት አጥሮት አንድ ቀን ሲበቀል
በሚያልፈው በዚህ ዓለም እንዴት ተስፋ ይጣላል
ሸመቆ አይደል አንድቀን ይከዳል
የልብ ጓደኛህ እስከሞት የሚወድ
ኢየሱስ ብቻ ነው እውነት ሕይወት መንገድ
አዝማች · Chorus
ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ
ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ
በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ
ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው
እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው
እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ይኼ ነው አምላኬ የተመማነኩበት
ይኼ ነው ጌታዬ ልቤን የጣልኩበት (፪x)
ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ይመከር
እውነት ሕይወት መንገድ የለም ከእርሱ በቀር (፪x)
እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው
እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ