Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብቻውን ጌታ ነው

Bechawen Gieta New

2011 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንደበት ኖሯቸው ምድርና ሰማይ

ምነው ቢናገሩ እንደሌለው መሳይ (፫x)

እኔስ በዚች ቃሌ በትንሿ አንደበት

አልወጣልህ አለኝ ዘምሬ የእርሱን ምህረት

ያምላኬን በጐነት (አሃሃ) የአምላኬን ቸርነት

ጥሩ ቃል ተመርጦ ዜማ ቢደረደር

በመልካም አዋቂ አምሮ ቢቀናበር

ልሳን ያለው ሁሉ ለአፍታ ሳያባራ

አይበቃም ቢዘመር ስለእርሱ ቢወራ (፪x)

(አሃሃ) ብቻውን ጌታ ነው ፤ (አሃሃ) መለኪያ የለውም

(አሃሃ) ፍጥረት ይራመዳል ፤ (አሃሃ) እርሱ እንደሚለው

(አሃሃ) ይገድላል ያድናል ፤ (አሃሃ) ይሾማል ይሽራል

(አሃሃ) ዐይኖቹን እይታ ፤ (አሃሃ) ማን ሸሽቶ ይሰወራል

ሄይ (፮x) ጌታ ነህ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

ሄይ (፮x) ኤልሻዳይ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

አስፈሪው ማዕበል ወጀብ ታዘዘለት

ተራራው ለክብሩ ዝቅ ዝቅ አለለት

ብቻውን ኤልሻዳይ በሃይል ይገዛል

ቢወድም ባይወድም ፍጥረት ይታዘዛል (፪x)

ሄይ (፮x) ጌታ ነህ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

ሄይ (፮x) ኤልሻዳይ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

check this section again

አጥቢያ ኮከብ ቆመው ፊቱ ሲዘምሩ

ሰማያት ሲሰግዱ ሲሞሉ በክብሩ (፫x)

መስፈሪያም ሲለካ ዙሪያዋን ሲገምት

ማን ነበር ያገዘው ምድርን ሲመሰርት (፫x)

በአደባባዮች ላይ ክህደት ሲዘመር

ያወቀ ሲመስለው ሰው ብዙ ሲናገር

የለም ያሉት ሄዱ ከነኮተታቸው

የእኛ አምላክ ግን አለ በዙፋኑ ይኸው (፪x)

(አሃሃ) ብቻውን ጌታ ነው ፤ (አሃሃ) መለኪያ የለውም

(አሃሃ) ፍጥረት ይራመዳል ፤ (አሃሃ) እርሱ እንደሚለው

(አሃሃ) ይገድላል ያድናል ፤ (አሃሃ) ይሾማል ይሽራል

(አሃሃ) ዐይኖቹን እይታ ፤ (አሃሃ) ማን ሸሽቶ ይሰወራል

ሄይ (፮x) ጌታ ነህ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

ሄይ (፮x) ኤልሻዳይ ብንለው

ሄይ (፮x) ሲችል ስላየነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ