ሚስጥር
Mister
2011 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሚስጥር አለ ልቤ (ሚስጥር ሚስጥር)
ለሰው ያልነገርኩት (ሚስጥር ሚስጥር)
አብረውኝ ለበሉ (ሚስጥር ሚስጥር)
ያላጨዋወትኩት (ሚስጥር ሚስጥር)
ዙሪያዬ ጸጥ ሲል (ሚስጥር ሚስጥር)
በሮቼን ዘግቼ (ሚስጥር ሚስጥር)
ልንገረው ለአምላኬ (ሚስጥር ሚስጥር)
የሆዴን ገልጬ (ሚስጥር ሚስጥር)
እዩት ይሄ ልቤን እየተሸከመ
ብቻውን አምቆት ብቻውን ታምኖ
ዛሬ ዙፋኑ ስር ሸክሜን ልጣለው
እስከመቼ ልዘን አምላክ እንደሌለው
ወዳጅ እንደሌለው
አዝማች · Chorus
ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት
መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት
በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለካስ አለጉዳይ (ሚስጥር ሚስጥር)
ለሰው የማይነግሩት (ሚስጥር ሚስጥር)
ወይ በሆድ ደብቀው (ሚስጥር ሚስጥር)
የማያባብሉት (ሚስጥር ሚስጥር)
አምቄ ደብቄ (ሚስጥር ሚስጥር)
እስከመቼ ልጐዳ (ሚስጥር ሚስጥር)
ልንገረው በእምባዬ (ሚስጥር ሚስጥር)
ሰምቶ ለሚረዳ (ሚስጥር ሚስጥር)
መጐዳቴን አይቶ ዘምበል ይልልናል
ሰምቶ እንዳልሰማ መቼ ጥሎ ያልፋል
ለእርሱ እነግረዋለሁ አልፈልግም ለሰው
የልቤን ዘርግፌ እገላገላለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት
መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት
በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (፪x)
ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት
መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት
በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ