ቀን አለ
Qen Ale
2011 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያሰቡት ሳይሰምር ሲቀር ሆኖ እንደህልም
በእኩለ ቀንም ላይ በጊዜ ሲጨልም (፪x)
በዕድሜ ያከማቹት በዋዛ ሲበተን
በመከራ እሳት ማንነት ሲፈተን (፪x)
ሁኔታውን ሳይሆን ቃልህን አምናለሁ
ታድናለህ ብዬ ስንቴ ዘምሬያለሁ
ወጀቡ ቢበዛም በአንተ ተስፋ አልቆርጥም
ይዘንባል እላለሁ ደመናውን ባላይም
አዝማች · Chorus
(ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች
ቁጥር 2 · Verse 2
(ቀን አለ) ይኸ ሌሊት ያልፋል
(ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ
(ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል
(ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል
(ቀን አለ) እሸጋገራለሁ
(ቀን አለ) በአስጨነቀኝ እራስ ላይ
(ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ (፪x)
የሕይወት ቀመሩ መውረድና መውጣት
ነፍሴ ምድረበዳው ውጊያው ቢያሰለቻት
ዓይኖቼ ሳይወዱ ተገደው ቢያለቅሱ
የድል መዝሙሮቼ ለዛሬ ቢረሱ
እንደማያልፍ የለም ይህን ቀን አልፋለሁ
ጌታዬ ሲመጣ በድል እወጣለሁ
ይህ ሰው አበቃለት ያለው ጠላቴ ነው
በቆፈረው ጉድጓድ ሲወድቅ አየዋለሁ
አዝማች · Chorus
(ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች
ቁጥር 3 · Verse 3
(ቀን አለ) ይሄ ሌሊት ያልፋል
(ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ
(ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል
(ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል
(ቀን አለ) እሸጋገራለሁ
(ቀን አለ) ባስጨነቀኝ እራስ ላይ
(ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ
በወይን ሃረግ ፍሬ ቢታጣ የሚቀመስ
ምንም እንኳን ዛሬ ባታፈራ በለስ (፪x)
በጐች ከማደሪያው ከበረት ቢታጡ
እርሾችም ጠውልገው መብልን ባይሰጡ (፪x)
እኔ ግን በእግዚአብሔር በእርሱ ደስ ይለኛል
በከፍታዎችም ላይ ያራምደኛል
በመድሃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ
ጌታ እግዚአብሔር ዘወትር ሃይሌ ነው
አዝማች · Chorus
(ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች
ቁጥር 4 · Verse 4
(ቀን አለ) ይሄ ሌሊት ያልፋል
(ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ
(ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል
(ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል
(ቀን አለ) እሸጋገራለሁ
(ቀን አለ) ባስጨነቀኝ እራስ ላይ
(ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ (፪x)
(ቀን አለ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ