ይታይ
Yetay
2011 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እረጭ ጸጥ ባለው በሙታን መንደር
ሕይወት የሚሰጠው ጌታ ተሰማ (፬x) ተሰማኝ ሲናገር
አልዓዛር ሆይ ውጣ ብሎ በድኑን ጠራው
አንድ ጌታ አለ በምድር በሰማይ ሙታን የሚሰማው
የመሞቱ ዜና በሮ የደረሳቸው
ከንቱ ምሥጋና ነው??? ሳይደርቅ እምባቸው
ፈጥኖ እንደደረሰ አምላኩ ከሰማይ
ምስኪን እንደማይቀር ለዓለም ሁሉ ይታይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይታይ (፫x) በክንዱ ደግፎ
ይታይ (፫x) እንደሚያቆም አቅፎ
ይታይ (፫x) መቃብር ይከፍታል
ይታይ (፫x) የሞተውን ያስነሳል/አልዓዛር ተነስቷል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
(ተነሳ) ሰዎች የከደኑት
(ተነሳ) የድንጋይ መቃብር
(ተነሳ) የማይሆነው ሊሆን
(ተነሳ) ሊሰራበት ተዐምር
(ተነሳ) ሊከብር ወዶ ነው
(ተነሳ) በሞቱ ሊወደስ
(ተነሳ) አልዘገየም ነበር
ኢየሱስ አልዓዛር ሲገነዝ
የደረቁት አጥንቶችን ሕይወት ዘርተው
ፍጥረት ታየኝ??? ለአምላኩ ምን ሊሳነው
መከራውን ከላዩ አራግፎታል
በእርሱስ ድንኳን ዘለዓለም ይዘመራል (፪x)
አዝማች · Chorus
ይታይ (፫x) በክንዱ ደግፎ
ይታይ (፫x) እንደሚያቆም አቅፎ
ይታይ (፫x) መቃብር ይከፍታል
ይታይ (፫x) የሞተውን ያስነሳል/አልዓዛር ተነስቷል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔም ታሪክ አለኝ አላዓዛርን መሳይ
በሞተው ነገሬ አምላክ ክብሩን ሲያሳይ
አራት ቀን አለፈው በቃው ሲባል ሸቶ
ትንሴ ዘራበት መቃብሬን ከፍቶ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይታይ (፫x) በክንዱ ደግፎ
ይታይ (፫x) እንደሚያቆም አቅፎ
ይታይ (፫x) መቃብር ይከፍታል
ይታይ (፫x) የሞተውን ያስነሳል/አልዓዛር ተነስቷል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
(ተነሳ) ሕይወት የሚሰጠው
(ተነሳ) ይህ ቃሉ ተሰማኝ
(ተነሳ) ከሙታን መካከል
(ተነሳ) ውጣ ብሎ ጠራኝ
(ተነሳ) ከመንፈሱ እስትንፋስ
(ተነሳ) ሕይወት እፍ አለብኝ
(ተነሳ) ነፍስ የዘራባቸው
(ተነሳ) እግሮቼም ቆሙልኝ
የደረቁት አጥንቶችን ሕይወት ዘርተው
ፍጥረት ታየኝ ለአምላኬ ምን ሊሳነው
መከራዬን ከላዬ አራግፎታል
በእኔ ድንኳን ዘለዓለም ይዘመራል (፪x)
በእኔ ድንኳን ዘለዓለም ይዘመራል (፪x)
አዝማች · Chorus
ይታይ (፫x) በክንዱ ደግፎ
ይታይ (፫x) እንደሚያቆም አቅፎ
ይታይ (፫x) መቃብር ይከፍታል
ይታይ (፫x) የሞተውን ያስነሳል/አልዓዛር ተነስቷል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ይታይ ይታይ ይታይ (፯x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ