ቢበራማ
Biberama
2018 · ትራክ 8 · 5:55 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመንገዴ ስሄድ ስራመድ በሕይወት ጐዳና
እግሮቼ በቤትህ ጸንተው ዓይኔ ግን ሳይበራ
የሚሄደው የሚመጣው ሲያዳክመው ልቤን
የቆምኩኝ ያለሁኝ መስሎኝ እያንገዳገደኝ
አልገባኝም ነበር የልቦና ዓይኔ ታውሮ
ምድር ምድር አለ የከበረውን ሰማይን ጥሎ
አዝማች · Chorus
ቃልህን ስሰማ ልቤ ተደስቶ
ለጊዜው ነበረ በስሜት ተገፍቶ
ነፋስና ጐርፉ ሊፈትነኝ መጣ
ይታወቀኝ ጀመር ከመንገድ ስወጣ
ቢበራማ በቃልህ ቢጸና ዓይኔ ቢበራ
ቢበራማ ጸንቶ ይቆም ነበር ፍሬ እያፈራ
ቢበራማ ቅርንጫፍ ከግንዱ ከተጣበቀ
ቢበራማ ያስታውቃል መልኩ አንተን ያወቀ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓይኖቼን አብራ ክፈት ዓይኔን
እነደ እኔ ሳይሆን እንዳንተ እንዳይ
በመንገዴ ስሄድ ስራመድ በሕይወት ጐዳና
እግሮቼ በቤትህ ጸንተው ዓይኔ ግን ሳይበራ
የሚሄደው የሚመጣው ሲያዳክመው ልቤን
የቆምኩኝ ያለሁኝ መስሎኝ እያንገዳገደኝ
አልገባኝም ነበር የልቦና ዓይኔ ታውሮ
ምድር ምድር አለ የከበረውን ሰማይን ጥሎ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሲዘነጋ ለቤ የሰማዩን ቤቱን
በዚህ ምድር ሲኖር እንግዳ መሆኑን
አይጐመጅም ነበር ለምድራዊው ኑሮ
የሰማዩን ዓለም አንዴ ቢያየው ኖሮ
አዝማች · Chorus
ቢበራማ የተጠራበትን የክብር ተስፋ
ቢበራማ የዘላለም እርስት ከቶ ማይጠፋ
ቢበራማ ዓይኖቼ ተከፍቶ ይህንን ቢያይ
ቢበራማ ይናፍቃል ልቤ ወደ ሰማይ
ቁጥር 4 · Verse 4
ዓይኖቼን አብራ ክፈት ዓይኔን
እነደ እኔ ሳይሆን እንዳንተ እንዳይ
ልመናዬ ይሄ ነው
አብራው ዓይኔን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ