ዝምታው
Zemetaw
2018 · ትራክ 10 · 5:59 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሚነጋ አይመስልም ሌሊቱ ረዝሞ
ጨለማውን አይቶ
ሌሊቱም ያልፋል ደግሞም ይነጋል
ብርሃን ተክቶ
አይዘኝ ሃሳብ ትካዜ
ይሆናል ሁሉ በጊዜ (፪x)
አትጠጉት በቃ ድንጋይ አድርጉበት ሸትቷል መቃብሩ
ጠብቀነው ነበር በጊዜ እንዲመጣ አክትሟል ነገሩ
ሰው ደክሞት ሲጨርስ ኢየሱስ እርሱ ይጀምራል
በሞተ ነገር ላይ ይፈርዳል ሕይወት ይሰጠዋል
ዝምታው ቢያስገርም የማያይ ቢመስልም
አይቸኩል እንደ ሰው ይፈርዳል በጊዜው
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
ሚነጋ አይመስልም ሌሊቱ ረዝሞ
ጨለማውን አይቶ
ሌሊቱም ያልፋል ደግሞም ይነጋል
ብርሃን ተክቶ
አይዘኝ ሃሳብ ትካዜ
ይሆናል ሁሉ በጊዜ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልቧ ያዘነባት ሁሌ ምታለቅሰው ልጅ የሌላት ሃና
ታሾፍባት ነበር ነገ የሚሆነው ያልገባት ፍናና
በጊዜው ፈረደ አምላኳ እንባዋን አበሰ
ትውልድ የሚያወሳው ልጅ ሰጣት ሕይወቷ ተካሰ
ዝምታው ቢያስገርም የማያይ ቢመስልም
አይቸኩል እንደ ሰው ይፈርዳል በጊዜው
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
አንዳንዶች እንደዚህ ናቸው
መከራው ሲበዛባቸው
እምነታቸውን ሲጥሉ
አይሰማም አያይም ሲሉ
አለ ሁሉንም የሚያይ
ከላይ ከሰማይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ስለዚህ አትታበዩ
በኩራት አትናገሩ
እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል
ይፈርዳል ይፈርዳል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ