Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የመዳኔ ነገር

Yemedanie Neger

2018 · ትራክ 3 · 5:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ደግሜ ደግሜ ብደጋግም

የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር

አሁንም መልሼ ብደጋግም

የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር

የመዳኔ ነገር

ቀሎ ስለመጣ አይቀልም በሕይወቴ የመስቀሉ ስራ

በክብር ታጅቦ ይመጣል ሊወስደኝ አርጐኛል ሙሽራ

ሰማይ ደስታ ሆነ ዕልልታው ቀለጠ በእኔ መዳን

እንዴት መታደል ነው በበጉ ዙፋን ፊት ከእርሱ ጋር መሆን

አጋንንት ቢወጣ ሽባ ቢተረተር

የሞተ ቢነሳ ይህም ያልፋል ምድር

አይወዳደርም ይሄኛው ተአምር

የመዳኔ ነገር

ደግሜ ደግሜ ብደጋግም

የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር

አሁንም መልሼ ብደጋግም

የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር

የመዳኔ ነገር

አማኝ ሞት አይፈራ እንግዳ ነውና በዚህ ምድር ላይ

ይናፍቃል እንጂ ከአምላኩ ጋር መኖር በላይ በሰማይ

ሰው ዓለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል መቼ ይጠቅመዋል

ከክርስቶስ ጋራ ለዘላለም መኖር ከሁሉም ይበልጣል

ጠላቴ ሆይ ስማ ሞኝህን አስፈራራ

ሞት አይፈራም አማኝ ሰማይ የእርሱ ስፍራ

ይሄ አለኝ ብዬ ቁሳቁስ አልቆጥር

የእኔ ሃብት ይሄ ነው ሞትን የሚሻገር

የመዳኔ ነገር

ክብር ቢሆን ያልፋል

ዝና ቢሆን ያልፋል

ጉልበት ቢሆን ያልፋል

ሃዘን ቢሆን ያልፋል

ማግኘት ቢሆን ያልፋል

ማጣት ቢሆን ያልፋል

የማያልፈው አንድ ነገር

በሰማያት ያለ ክብር

ተጽፎልኝ ስሜ በላይ

ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ

በዚህ ነው የእኔ ደስታ

ሞልቶኛል ዕልልታ

ለዚህ ነው ጩኸቴ

ሰማይ ቤት በመግባቴ

ክብር ቢሆን ያልፋል

ዝና ቢሆን ያልፋል

ጉልበት ቢሆን ያልፋል

ሃዘን ቢሆን ያልፋል

ማግኘት ቢሆን ያልፋል

ማጣት ቢሆን ያልፋል

የማያልፈው አንድ ነገር

በሰማያት ያለ ክብር

ተጽፎልኝ ስሜ በላይ

ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ