አባት አለኝ
Abat Alegn
2018 · ትራክ 9 · 6:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አባት አለኝ አባት
ሁል ጊዜ የምመካበት
ሚረዳኝ ሚራራልኝ
ከጐኔ የማይለየኝ
ምሕረቱ የበዛ በሕይወቴ
ያሳደገኝ ከልጅነቴ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምሕረቱ ያቆመኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
አይተኛም እርሱ እኔን እየጠበቀ
ከክፉ አውሬ እየተናጠቀ
ያሳድረኛል በለምለሙ ስፍራ
በእጆቹ ይዞኛል ክፉን እንዳልፈራ
ላምልክህ ወድጄ እጆቼን አንስቼ
መልካምነትህ አይተዋል ዓይኖቼ
ውሰድ አምልኮዬን መስዋዕቴን
ዛሬም አይሰለቸኝ አንተን ማመስገን
አዝማች · Chorus
የወደቀውን ሰው አንስቶ
አስውቦ ታሪኩን ለውጦ
በምሕረትህ ቆሞ እንደገና
ይዞ መጥቷል በዙ ምሥጋና
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ
ባለውለታዬ ክበር እግዚአብሔር
ቁጥር 3 · Verse 3
አባት አለኝ አባት
ሁል ጊዜ የምመካበት
ሚረዳኝ ሚራራልኝ
ከጐኔ የማይለየኝ
ምሕረቱ የበዛ በሕይወቴ
ያሳደገኝ ከልጅነቴ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምሕረቱ ያቆመኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
የደከመውን በፍቅር ሚያነሳ
ሰው የረሳውን ከቶ የማይረሳ
ይቅርታው ብዙ እንደ ሰው አይፈርድ
እውነተኛ አባት ልጆቹን ሚወድ
ላምልክህ ወድጄ እጆቼን አንስቼ
መልካምነትህ አይተዋል ዓይኖቼ
ውሰድ አምልኮዬን መስዋዕቴን
ዛሬም አይሰለቸኝ አንተን ማመስገን
አዝማች · Chorus
የወደቀውን ሰው አንስቶ
አስውቦ ታሪኩን ለውጦ
በምሕረትህ ቆሞ እንደገና
ይዞ መጥቷል በዙ ምሥጋና
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ
ባለውለታዬ ክበር እግዚአብሔር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ