ከኖሩማ
Kenoruma
2018 · ትራክ 5 · 5:34 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ንፋሱ ነፈሰና አለፈ
ወጀቡም ጸጥ አለ አለፈ
መንገዴን ዞር ብዬ ሳየው
ይህ ሁሉ ለመልካም የሆነው
ስላለ ጌታ አጠገቤ
ስላለ አባ አጠገቤ
ከኖሩማ ኑሮ ከአንተ ጋራ
በችግር ቢሆን በመከራ
አዝማች · Chorus
ከተያዘም እጄ በአንተ እጅ
ሕይወቴ ሰላም ነው የሚመች
ስሄድ ከአንተ ጋራ በሕይወት መንገድ
ምንም ነገር አይሆን ያለ አንተ ፈቃድ
አያስጨንቀኝም ነገ የሚሆነው
የነፍሴ ፍጻሜ በእጅህ ነው
የእኔ ነገር ሰው የማይዘጋው ሰው የማይከፍተው
ሁሉ በእጁ ነው
የእኔ ነገር መጀመሪያዬ መጨረሻዬ
በእርሱ አይደል ወይ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከኖሩማ ኑሮ ከአንተ ጋራ
በችግር ቢሆን በመከራ
ከተያዘም እጄ በአንተ እጅ
ሕይወቴ ሰላም ነው የሚመች
ሲጸልይ ዳንኤል አንተን ስለጠራ
ጉድጓድ ውስጥ ከተቱት በአንበሳ እንዲበላ
ይንከባከቡታል እንኳን ሊበሉት
ችግር ይቀየራል በምቾት
የእኔ ነገር ሰው የማይዘጋው ሰው የማይከፍተው
ሁሉ በእጁ ነው
የእኔ ነገር መጀመሪያዬ መጨረሻዬ
በእርሱ አይደል ወይ
ቁጥር 3 · Verse 3
ቆይ ምን አለ ከአንተ የራቀ የተሰወረብህ
እኮ ምን አለ አልፋ ኦሜጋ ሁሉን የምታውቅ
ቆይ ምን አለ ድንገት ተገልጦ የሚያስደነግጥህ
እኮ ምን አለ ሰማይ ምድሩን ሁሉን በእጅህ ይዘህ
መላ ሕይወቴ አምላኬ ሁሉ በእጅህ
እድሜ ዘመኔ አምላኬ ሁሉ በእጅህ
ነገዬም ቢሆን አምላኬ ሁሉ በእጅህ
እስትንፋሴ እንኳን አምላኬ ሁሉ በእጅህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ