እጄን አነሳሁ
Ejien Anesaw
2018 · ትራክ 7 · 7:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልቤን ማዋየው የውስጤን ሚስጥረኛዬ
ባዝንም ብከፋም ማይለየኝ መጽናኛዬ
ነፍሴ ትረካለች በአንደበቱ ቃል በምክሩ
የመኖሬ ትርጉም እርሱ ብቻ ነው ሚስጥሩ
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ
የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ
ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ
የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ
እጄን አነሳሁ ወደ ላይ
ወደ ሚሰማኝ ወደሚያይ
ጩኸቴን ሰምቶ ይመልሳል
እንባዬን ከዓይኔ ያብሳል
አባትዬ አባትዬ አባብዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእስትንፋሴ ይልቅ ይቀርበኛል አይርቀኝም
የፍቅር ቃል ኪዳን ገብቶልኛል አይተወኝም
እንዳወራው ድፍረት ይሰጠኛል የፍቅር ዓይኖቹ
ልቤ ተፈወሰ ሲዳስሰኝ በመልካም እጆቹ
አዝማች · Chorus
መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ
መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
የልቤን ማዋየው የውስጤን ሚስጥረኛዬ
ባዝንም ብከፋም ማይለየኝ መጽናኛዬ
ነፍሴ ትረካለች በአንደበቱ ቃል በምክሩ
የመኖሬ ትርጉም እርሱ ብቻ ነው ሚስጥሩ
አዝማች · Chorus
ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ
የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ
ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ
የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ
እጄን አነሳሁ ወደ ላይ
ወደ ሚሰማኝ ወደሚያይ
ጩኸቴን ሰምቶ ይመልሳል
እንባዬን ከዓይኔ ያብሳል
አባትዬ አባትዬ አባብዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
ትዋሽ ዘንድ እንደሰው አይደለህ እውነተኛ ነህ
የተናገርከውን ታደርጋለህ ትፈጽማለህ
ቢታመኑህ ታማኝ አንተ ብቻ ወረት የሌለህ
ከአጠገቤ ሁሌ ማትለየኝ አንተ ብቻ ነህ
አዝማች · Chorus
መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ
መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትልቅነትህ እየገረመኝ
አጠገቤ ነህ ይሄም ሲደንቀኝ
ዘልቀህ ውስጤ ገብተሃል
መኖሪያህን አድርገሃል
የእኔ ሆነሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ