ደሞ ተነሳ
Demo Tenesa
2018 · ትራክ 6 · 6:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይውለቅ ከላዬ ላይ ይህ የክብር ልብሴ
በፊቱ ላሸብሽብ ታመስግነው ነፍሴ
አይገደኝም እኔ ያሉኝን ቢሉኝ
ታቦቱ ከፊቴ ቤቴ ቀርቦልኝ
አዝማች · Chorus
ክብር ይሁን ክብር ይሁን
ክብር ይሁን ክብር ይሁን
ደግሞ ተነሳ ልቤ እንደገና
ከየት እንዳነሳኝ ትዝ አለኝና ትዝ አለኝና
አልቻልኩበትም ዝም ማለት
ምሥጋናና ክብር ይሁንለት ይሁንለት
ምሥጋናና ክብር ይሁንለት ይሁንለት
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ ሆይ ባርኪው አምላክሽን
ከወደቅሽበት ያነሳሽን
ውለታውን እንዳትረሺ
ለምሥጋን ሁሌ ተነሺ
ማን ነበረ ያኔ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
በበረሃው ላይ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
እየደጋገፈ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
ያም ዘመን አለፈ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
አምልኮዬን ይዤ አደባባይ ልውጣ
ያኮራኛል እንጂ አላፍርም በጌታ
የረዳኝ ይክበር ጌታዬ '
ያገዘኝ ይክበር ጌታዬ
አዝማች · Chorus
ደግሞ ተነሳ ልቤ እንደገና
ከየት እንዳነሳኝ ትዝ አለኝና ትዝ አለኝና
አልቻልኩበትም ዝም ማለት
ምሥጋናና ክብር ይሁንለት ይሁንለት
ምሥጋናና ክብር ይሁንለት ይሁንለት
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአዳኝ ወጥመድ እያስመለጠ
እባቡን ጊንጡን እያስረገጠ
እኔ ያልዘመርኩኝ ማን ሊዘምር
ተደርጐልኝ ብዙ ተዓምር
ማን ነበረ ያኔ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
በበረሃው ላይ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
እየደጋገፈ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
ያም ዘመን አለፈ እርሱ አይደለም ወይ ከጐኔ ሆኖ ያበረታኝ
አምልኮዬን ይዤ አደባባይ ልውጣ
ያኮራኛል እንጂ አላፍርም በጌታ
የረዳኝ ይክበር ጌታዬ '
ያገዘኝ ይክበር ጌታዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
እዩአት ስትከፋ ሜልኮል
በአምላኬ ፊት ሳሸበሽብ
ውርደት መስሏት ክብሬን መጣሌ
በእርሱ አይደል ወይ በሕይወት መኖሬ
ሰማይን ለሰራ ምድርን ለዘረጋ
ላለና ለሚኖር አልፋና ኦሜጋ
ከዚህ በላይ እሆናለሁ
ገና ገና እሆናለሁ
አባቴ ነው እሆናለሁ
እወደዋለሁ እሆናለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
እዩአት ስትከፋ ሜልኮል
በአምላኬ ፊት ሳሸበሽብ
ውርደት መስሏት ክብሬን መጣሌ
በእርሱ አይደል ወይ በሕይወት መኖሬ
ሰማይን ለሰራ ምድርን ለዘረጋ
ላለና ለሚኖር አልፋና ኦሜጋ
ከዚህ በላይ እሆናለሁ
ገና ገና እሆናለሁ
አባቴ ነው እሆናለሁ
እወደዋለሁ እሆናለሁ
ሕይወቴ ነው እሆናለው
ኣ...
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ