Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቤዛ የሆንክልኝ

Bieza Yehonkelegn

ትራክ 3 · 5:03 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ

የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ

ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን

ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (፪x)

በወርቅ ይሁን በብር ፣ በጥበብ ፣ በዕውቀት

የዳነ ማን አለ ከኃጢአት ውድቀት?

ጌታ ሆይ ! አንተ ነህ ጽድቅን ያለበስኸኝ

በምሕረት አማልደህ ከዓብ ያስታረቅኸኝ (፪x)

ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ

የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ

ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን

ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (፪x)

በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ

ከዘለዓለም ሞት ዳንኩኝ ከመከራ

በነጻ ታድዬ የጽድቅን ሥጦታ

ምሥጋና እሰዋለሁ ለተቤዠኝ ጌታ (፪X)

ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ

የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ

ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን

ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (፪x)

ብላቴንነቴን ፣ ድካሜን ገምተህ

አንተ ብርቱ ጌታ በእኔ ላይ ተገልጠህ

የበረታብኝን ጠላቴን ቀጥቅጠህ

ድል ያጐናተጸፍኸኝ ኢየሱስ አንተ ነህ (፪x)

ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ

የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ

ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን

ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (፪x)

መልካሙን ሥራህን በሕይወቴ ፈጽመህ

እንድትታይብኝ በኑሮዬ ጐልተህ

ይህ ነው ልመናዬ የዘወትር ጸሎቴ

ክብሬ ፣ ዕርካታዬ ፣ አንተ ነህ ትምክህቴ (፪x)

ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ

የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ

ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን

ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ