የኃጢአተኛውን ጥፋት
Yehatiategnawn Tefat
ትራክ 2 · 3:29 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሕረትና ዕውነት ፣ ፍቅር ቸርነት ከሞላው ጌታ
ኃጥዕ በንስሐ ይቀበል ይቅርታ
ማንም እንዳይጠፋ መድህን ሞቶልናል
ክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛ ሆኖልናል
አዝማች · Chorus
የኃጢአተኛውን ጥፋት
እግዚአብሔር መቼ ይወዳል?
የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በምክሩ ያስባል ፣ በምክሩ ያስባል
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው ግን በውድቀቱ
ለምን ተስፋውን ይቆርጣል ቶሎ?
ለምን ይቀናዋል መውረድ አሽቆልቁሎ?
"ጌታን እጠብቃለሁ ፣ ቢገድለኝም" ብሎ
በዕምነት የሚቆም አይቀርም ጐስቁሎ
አዝማች · Chorus
የኃጢአተኛውን ጥፋት
እግዚአብሔር መቼ ይወዳል?
የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በምክሩ ያስባል ፣ በምክሩ ያስባል
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚወደውን ልጅ እግዚአብሔር ለጥቅሙ ይቀጣዋል
መክሮ ይገስጸዋል ፣ ያስተካክለዋል
በአባትነት ዓይኑ ይመለከተዋል
ሲፍገመገም ቢያየው ፣ ፍጥኖ ይደግፈዋል
አዝማች · Chorus
የኃጢአተኛውን ጥፋት
እግዚአብሔር መቼ ይወዳል?
የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በምክሩ ያስባል ፣ በምክሩ ያስባል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ