ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
Qalun Keto Yemayatef
ትራክ 4 · 4:17 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
ቁጥር 1 · Verse 1
የኃጢአትን ከተማ ፣ የዲያብሎስን ሥራ
ሲያፈራርሰው አይተናል ያን ምሽግ ያንን ተራራ
ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ ፣ የሕይወታችን ብርሃን
የተስፋ ቃሉን ፈጸመው በሞቱ እኛን በማዳን
አዝማች · Chorus
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰላምና በሕይወት ፣ በበጐ ነገርም ምክር
አበሳችን እንዲወገድ ፣ እሮሮአችንም እንዲቀር
በእኛ ያለውን ነገር ጌታ እግዚአብሔር አይቶ
ቀንበራችንን ሰበረው ለቅሶአችንን እርሱ ሰምቶ
አዝማች · Chorus
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
ቁጥር 3 · Verse 3
የሲኦልን ማስፈራራት ፣ የመከራን አውሎ ነፋስ
የኃያላኑን ጭካኔ ፣ የቁጣቸውን እስትንፋስ
የማዕበሉን ሁሉ ጩኸት ፣ የዓመጽንም ዝማሬ
በሥልጣኑ ቃል ገስጾ ዝም አሰኝቶታል ዛሬ
አዝማች · Chorus
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
ቁጥር 4 · Verse 4
የመማጸኛ ግንብ ነው ፣ የድሆች ሁሉ መጠጊያ
ምቹ መሸሸጊያ ዓለት የለንም ከኢየሱስ ወዲያ
ብዙዎቹም ይድናሉ ገብተው ከዚህ መጠለያ
ስለሚሆንልን ሁሉ ይክበር ጌታ ፣ ሃሌሉያ!
አዝማች · Chorus
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ