ኢየሱስ ክርስቶስ
Eyesus Kerestos
ትራክ 11 · 6:22 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክርስቶስ
ትላንትናም ዛሬ
እስከ ለዘለዓለም
ያው ነህ (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማያት አርጅተው ከምድር ጋር ሲያልፉ
በውስጣቸው ያሉት ኃይላትም ሲጠፉ
አንተ ግን አቤቱ ለዘለዓለም ያው ነህ
መለወጥ ሳያሻህ ደምቀህ ትኖራለህ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክርስቶስ
ትላንትናም ዛሬ
እስከ ለዘለዓለም
ያው ነህ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኛ የምናመልከው ሳይታክት ሳይደክም
በሥልጣኑ ገኖ ይኖራል ዘለዓለም
አልፋ ነው ኢየሱስ ዖሜጋም ነው ጌታ
በበረቱብን ላይ ክንዱ የበረታ
ሃሌ ሉያ! ሃሌ ሉያ! ሃሌ ሉያ!
ተጠብቀናል ታማኝ በሆነው
ኢየሱስ በአንተ ጉያ
ገና ኃጢአተኞች በደለኞች ሳለን
የእግዚአብሔርን ፍቅር በክርስቶስ አየን
በመስቀል ላይ ሞቱ የእኛን መርገም ወስዶ
ጽድቁን አልብሶናል ማቃችንን ቀዶ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ክርስቶስ
ትላንትናም ዛሬ
እስከ ለዘለዓለም
ያው ነህ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በእኛ ላይ ያለው ከጥንትም ያሰብከው
ዛሬም እንዳየነው ዓላማህ ፍቅር ነው
በክንፎችህ ጥላ ኖረናል ተማምነን
በድል እንዘልቃለን በእጆችህ ተይዘን
ሃሌ ሉያ ! ሃሌ ሉያ ! ሃሌ ሉያ !
ተጠብቀናል ታማኝ በሆነው
ኢየሱስ በአንተ ጉያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ