ከዚህም የሚበልጥ
Kezihem Yemibelt
ትራክ 12 · 3:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና ፣ የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ ፣ በጌታ ምሥጋና
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ በመንፈሱ በቅሉ መርምሮ
ሥራችንን ሁሉ ቢነግረን ዘርዝሮ
በዕውቀቱ ተደንቀን ፣ በኑሮአችን አፍረን
ንስሐ ገብተናል "ይቅር በለን" ብለን
አዝማች · Chorus
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና ፣ የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ ፣ በጌታ ምሥጋና
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃጢአታችንን በደሙ አነጻው
የእኛ ጌታ ኢየሱስ ይቅርታው ብዙ ነው
ርኩስ መናፍስትን በኃይሉ ያስወጣል
በወንጌሉ ሥልጣን መንግሥቱን ያሰፋል
አዝማች · Chorus
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና ፣ የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ ፣ በጌታ ምሥጋና
ቁጥር 3 · Verse 3
"ጌታ ሆይ!" እያለ ለሚቃትተው
ማዳኑ ሊመጣ ጽድቁ ሊገለጥ ነው
የእግዚአብሔር ምሕረት ሁሉንም አብስሩ
የበረከት ዝናብ ይኸው ውሽንፍሩ
አዝማች · Chorus
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና ፣ የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ ፣ በጌታ ምሥጋና
ቁጥር 4 · Verse 4
ረሃብተኛ ሲመገብ ፣ ልኡል ቃሉን ሲሰጥ
በጻድቅን ዕልልታ ምድር ስትናወጥ
በምሥጋና ዜማ በደስታ ዝማሬ
በታላቁ መከር የአገልግሎት ፍሬ
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና ፣ የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ ፣ በጌታ ምሥጋና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ