አቤቱ ጌታችን
Abietu Gietachen
ትራክ 5 · 4:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ ጌታችን፣ እስኪ እናመስግንህ
ለውለታህ ምላሽ "ክበር" እንበልህ
ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ሽቶ
ዕምነት ተስፋችንን ሊያጨልም ዝቶ
አምርሮ ቢነሣም እጅግ ተቆጥቶ
ተገዝቶ አየነው በአንተ ድል ተነሥቶ
አዝማች · Chorus
ስለ ዕምነታችን ፣ ስለ ሕይወታችን
የተሟገትክልን ፣ ተመስገን ጌታችን
ቁጥር 2 · Verse 2
የተጓዝንበትን መንገድ ሊያቋርጥ
ጠላታችን አልፎ እንቅፋት ቢያስቀምጥ
የተመሸገውን ከፍ ያለውን ቅጥሩን
አፈራርሰህ ጣልከው ኢየሱስ ተመስገን
አንተ ቅን የሆነን መንገድ ታቀናለህ
የተዘጋውንም በር ትከፍትልናለህ
የሕዝብህን ስድብ ከምድር አስወግደህ
ከፊታቸውም ላይ እንባቸውን አብሰህ
ራሣቸውን በዘይት በሞገስ ቀብተህ
በምሥጋናቸውም አንተ ትነግሣለህ
አዝማች · Chorus
ለታናሹ መንጋ በዝቷል ቸርነትህ
ክበር አምላካችን ዘላለም ልዑል ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ግብዣን አዘጋጅተህ በክብር ጠራኸን
በንጉሥ ገበታ ይኸው አስቀመጥከን
በክርስቶስ ኢየሱስ በከበረው ሥፍራ
ነፍሣችን ጠገበች ከሕይወት እንጀራ
ፈቅደን ከልባችን እናመልክሃለን
ለዘለዓለሙም ለአንተ እንገዛለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ