Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የፀሎት ቤት ይሁን

Yetselot Biet Yehun

ትራክ 7 · 4:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

በልጅህ ደም "ሕይወት ሰላም ይሁን!" ብለህ

ለሐጢአታችን ይቅርታን አውጀህ

እግዚአብሔር ሆይ! ታረቅኸን ተመስገን

የክብርህ ማረፊያ መቅደስህ አደረግኸን (፪x)

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

ዙፋንህ በሰማይ የሆነ ንጉሥ

በምድር በእኛ መሃል ስምህ ይቀደስ

የመዓዛ ሽታ መሥዋዕታችንን

ምሥጋናን ተቀበል ከሕይወታችን (፪x)

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያሉ መላዕክት

በትጋት ሲያመልኩህ ቀንም ሆነ ሌሊት

ከእኛም ይድረስህ ውዳሴ ማሕሌት

ምልጃም ጸሎታችን ፣ ምሥጋና ስግደት (፪x)

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

መቅረዝህም ይንደድ ፣ ይታይ ብርሃንህ

የጸሎት ቤትህን ሙላው በክብርህ

አሕዛብም ይምጡ ወደ ጸዳልህ

ይስገዱልህ ድነው በቅዱስ ስምህ (፪x)

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

የዓለም ገበያ እንዳይሆን ማትረፊያ

ቀድሰህ ጠብቀው የአንተን ማደሪያ

የዘለዓለም ሕይወት ፈውስን መቀበያ

ይሁንልን ቤትህ የመንፈስ መኖሪያ (፪x)

የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ፣ ይኸ መቅደስህ

የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ፣ ይኸ መቅደስህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ