ፍቅር ነው የጐደለኝ
Feqer New Yegodelegn
ትራክ 10 · 3:58 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትንቢትና ዕውቀት መገለጥ ቢኖረኝ
ተራራን የሚያፈርስ ዕምነት ሁሉ ባገኝ
በሰዎች በመላዕክት ልሳን ብናገርም
ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር ይታገሳል ፣ ቸርነት ያደርጋል
በዕውነት ደስ ይለዋል ፣ ዓመጽን ይጠላል
አይቀናም ፣ አይመካም ፣ ራሱን ያዋርዳል
እየተበደለ ሁሉን ይቅር ይላል
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በአመቺ ቦታ ላይ ጠላቱን አግኝቶ
በመልካሙ : መንገድ በፍቅር ሸኝቶ
በሰላም የሚሰድ ከሰው ልጆች ማነው?
ዳዊት በዘመኑ ይህን አደረገው
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጠላቶችህ ሳለን ሞትህ ካስታረቀን
በመስቀል ላይ ፍቅርህ ሕይወት ከሰጠኸን
ሕይወት እንድናተርፍ ሰውን ሁሉ ወድደን
በዕውነተኛው ፍቅር ጌታ አጥለቅልቀን
አዝማች · Chorus
ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ
በደልን የምቆጥር ነኝ
ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ
መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ
በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ