Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቸር

Cher

ትራክ 6 · 6:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቸርነትህ ብዙ ነው አያልቅም ባወራው

እንደኔ ፍቅርህን ያዩ በምሕረትህ ውልው ያደሩ

ክበር ይሉሃል አንተን በዘምናት ያልተውከንን

ቸርነትህን ያዩ በምሕረትህ ውልው ያደሩ

ክበር ይሉሃል አንተን በዘምናት ያል ጣልከን

ቸር ነህና ምሕረትህ ለዘላለም

ለዘላለም እንዳንተ ያለ የለም

ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘላለም

ለዘላለም እንደ እግዚአብሔር የለም

ለፃድቁም ለኅጥኡ ፀሀይን አወጣህ

ላልተገባን ሁሉ ምህረትን አበዛህ

የሰው ልጅ በሙሉ ያንተ ጥገኛ ነው

ይነጋል ይመሻል ይህ ደግነትህ ነው

አመስግኑት ስገዱለት ክብር ስጡ ለእርሱ ምህረት

እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረው የማይተወው

ክብር ስጡ አመስግኑ ዘምሩለት እልል በሉ

እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረው የምያኖረው

ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘላለም

ለዘላለም እንደ እግዚአብሔር የለም

በቸርነት በምህረቱ ያልተረዳ የለም

በጎነቱ ብዙ እንደሰው አይደለም

በመልካምነቱ ስንቱን ተሻገረን

ያምይገፋውን በድል እያለፈን

አመስግኑት ስገዱለት ክብር ስጡ ለእርሱ ምህረት

እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረው የማይተወው

ክብር ስጡ አመስግኑ ዘምሩለት እልል በሉ

እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረው የምያኖረው

ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘላለም

ለዘላለም እንደ እግዚአብሔር የለም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ