ኃይሌም
Hailem
ትራክ 10 · 5:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በ"ይሁን!"ብቻ በቃልህ ብቻ ሰማይ ምድሩ ቀና
የስምህ ጉልበት የኃይልህ ችሎት ሁሉን አፀና
የሰው ክንድ የአንተን አይቋቋምም ከቶ ችሎ
አትገመትም አትጨረስም እንዲህ ነህ ተብሎ
ምን ቢሰበሰብ ኃይል
ቢመስል ሲታይ የሚያይል
አንተን ያመነህ ግን አይወድቅም
ካንተ ማንም አይቀድምም
የምድሩ ኃይል ተጠቅጥቆ
ቢያሰፈስፍ ሊታይ ልቆ
የፈጠርከው አይገዛህም!
ኃይል ያንተ ነው አይቻልም!
ቁጥር 2 · Verse 2
በስብርባሪ ደህና የደረሰ አለ ባንተ ጉልበት
ደሞም በጠጠር ኃያሉን ጥለህ አየን እንደዘበት
አበቃ ሲባል ያንተ ይጀምራል ያለገደብ
ከልካይ የለህም! ካሰብክ ልትሰራ አትወሰንም!
ምን ቢሰበሰብ ኃይል
ቢመስል ሲታይ የሚያይል
አንተን ያመነ ግን አይወድቅም
ካንተ ማንም አይበልጥም
የምድሩ ኃይል ተጠቅጥቆ
ቢያሰፈስፍ ሊታይ ልቆ
የፈጠርከው አይቀድምህም!
ካንተ ማንም አይበልጥም!
ቁጥር 3 · Verse 3
የኔ ኃይል ጥቂት ትንሽ ቢሆንም
የዙሪያዬ ድምፅ ጉልበት ቢያይልም
ያመንኩትን ክንድ ግን የለም ሚያክለው
አልናወጥም ኃይል የእግዚአብሔር ነው
እርሱ የዘጋውን የሚከፍት የለም
የለም ሚዘጋ የከፈተውንም
ብርቱ ክንድ አለው የማይለካ
የታመኑትን የማያስነካ
ብርቱ ክንድ አለው የማይነካ
የታመኑትን የማያስነካ
ቁጥር 4 · Verse 4
ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው
የኔ ጉልበት ሰማይና ምድርን ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው
አዝማች · Chorus
ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው!
ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው!
ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው!
ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ