አልፍ ዕዳ
Elf Eda
ትራክ 15 · 6:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምስጋና የሚሠዋ እርሱ ያከብረኛል
ማዳኔን የማሳይበት በዚያ ድል ይገኛል
ይህን ጌታ ብለሀልና
ይኸው ከልቤ ምስጋና
እግዚአብሔር የተገባህ
በምስጋና የተፈራህ
ባለፍኩበት መንገድ እጅህን ብዙ አየሁ
የውለታህን ቁጥር አልችልም ልገልፀው
ብዙ ብዙ ዋልህ ይህን አልዘነጋም
ያረግክልኝ ሁሉ ከልቤ አይጠፋም
አዝማች · Chorus
እልፍ ዕዳ አለብኝ የምስጋና
እልፍ ዕዳ አለብኝ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የዝማሬ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የውዳሴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ባያደርስልኝም የልቤን በሙሉ
ምስጋና ነው መልሴ ላረክልኝ ሁሉ
በመልካምነትህ ቤቴን ሞልተኸዋል
ከምስጋና በቀር ምን ብል ይገልፅሀል
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙ ዕዳ አለብኝ የምስጋናህ
ብዙ ዕዳ አለብኝ የውለታህ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የምስጋና
እልፍ ዕዳ አለብኝ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የዝማሬ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የውዳሴ
ቁጥር 4 · Verse 4
ካልተደረገልኝ ይልቅ የተደረገልኝ ስንቱ ነው
እኔ አልሆነልኝም ከምለው ይልቅ የሆነልኝ እጅግ ብዙ ነው
ዛሬም ጥያቄዬን ይዤ ለምስጋና ልቤ አይዘገይም
በስምህ ስንቱን አልፌያለሁ ይህንን ከልቤ አልፍቀውም
አዝማች · Chorus
እልፍ ዕዳ አለብኝ የምስጋና
እልፍ ዕዳ አለብኝ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የዝማሬ
እልፍ ዕዳ አለብኝ የውዳሴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ